Skip to content
zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Opens in a new window
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
Episodes
11
28 August 2026
በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ
በኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ እና ሰሜናዊ ክፍል አንዳንድ አከባቢዎች ላይ በክረምቱ በብርቱ የሚጠበቀው ዝናብ ባለመጣሉ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው አርሶአደሮች እና አርብቶ አደሮች ላይ ስጋት ማንዣበቡ ተነግሯል። በኢትዮጵያው ድርቅ አደጋው 165 ወረዳዎች ተለይተው ለምላሹ እየተሰራበት መሆኑን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገልጿል።
28 August 2026
ለሃገራቸውና ለማኅበረሰባቸው በጎ የሰሩ ግለሰቦች ሽልማት
የሃገራቸው እና የማኅበረሰባቸው ባለውለታዎች ናቸው የተባሉ ግለሰቦች፣ ዩናይትድስቴትስ ቴክሳስ ዳላስ ውስጥ ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጣቸው። ዘንድሮ ለዐሥረኛ ጊዜ በቴክሳስ ዳላስ በተካሄደው በዚሁ የምስጋና እና ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ፤በተለያዩ ዘርፎች ሽልማትና ዕውቅና የተሰጣቸው ዐሥር ግለሰቦች ናቸው።
28 August 2026
በአፋር ክልል የዝናብ መቅረትና የቀረጥ ጭማሪ አርብቶ አደሩን ፈትኖታል
በአፋር ክልል ባለፈው አንድ ዓመት በቂ ዝናብ ባለመገኘቱ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ በአርብቶ አደሮችና እንስሳቶቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። በተለይም በዳሊፋጌ እና በያንጉዲ ወረዳዎች የውሃና የመኖ እጥረት በመከሰቱ በርካታ አርብቶ አደሮች አካባቢያቸውን ለቀው ወደ አዋሽ ተፋሰስ በመሰደድ ላይ ናቸው።
28 August 2026
በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ምስራቃዊ ወረዳዎች ጥቃት
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡ በወረዳው ማክሰኞ ማለዳውን ተጀምሮ ቀኑን ውሎበታል በተባለው የታጣቂዎቹ ጥቃት ቢያንስ በአንድ ቀበሌ ብቻ ሰባት ሲቪል ሰዎች ስለመገደላቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
28 August 2026
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ያስመዘገበው ጃለል ግርማ
ጃለል ግርማ ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቀዋል። ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣም ጠብቆ ነበር። ያልገመተው ነገር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት እንደሚያስመዘግብ ነው።
28 August 2026
ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች ተቀጠሩ
"በአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው በእሥር ላይ የሚገኙትና ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች እና ጠበቃ ለቀጣዩ ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን ተቀጠሩ። ኢሕአፓ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለኢሰመኮ ጉዳዩን በደብዳቤ ያሳወቀ መሆኑን ገልጾ "ኹኔታው ተጣርቶ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥያቄ አቅርቧል።
27 August 2026
ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ብሔራዊ ምክክር የትኛዉን ተሞክሮ ትዉሰድ?
ኢትዮጵያዉያን ያካሄዱት ምክክር የሃገሪቱን የኃይል ፖለቲካ ወደ ዉይይት ባህል፤ ወደመደማመጥ ባህል ያመጣ ከፍተኛ ለዉጥ ነዉ ብለዉ ያስባሉ? የተገኙት የመፍትሄ ሃሳቦች በቀጣይ ተግባራዊ እንዴት ተግባራዊ ይደረጋሉ? በአፍሪቃ የትኞቹ ሃገራት ብሔራዊ ምክክርን አካሄዱ? የትኞቹ ተሳካላቸዉ? የትኞቹ ሃገራትስ አልተሳካላቸዉም? የትኛዉን ተሞክሮ እንዉሰድ?
02 August 2026
እንወያይ፤ ስደት፣ መንከራተት፣ ሞት ማቆሚያው የት?
ዓለም አቀፍ የጠፉ ስደተኞችን አፈላላጊ ድርጅት እንዳስታወቀው ደግሞ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2024 እስከ 2026 ባሉት ዓመታት በሜዲትራንያን ባሕርና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የስደት መስመሮች ቢያንስ 15,000 ስደተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ይፋ አድርጓል።
19 July 2026
ዉይይት፣ የአዲስ አበባ፣ የመቀሌና የአስመራ መሪዎች ዉዝግብ ንሯል፤ቀጥሎስ? ጦርነት ወይስ ሰላም?
የትግራይ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም፣ በምርጫም፣ በምክክር ጉባኤ፣ በአገራዊ የፖሊሲ ዉሳኔዎችም አለመካፈሉ ክልሉን በሚመራዉ በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ና በኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥት መካከል የተፈጠረዉ ጠብ እየተካረረ መምጣቱን መስካሪ መስሏል
12 July 2026
ሃገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ከተስፋ ባሻገር
ኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ጥቂት ቀናት ቀርተዋታል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምክክሩ ላይ ይሳተፋሉ የተባሉ ከአራት ሺ በላይ ተወያዮች አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ውጪ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከሶስት ዓመታት በላይ እንደወሰደበት ታይቷል።